በኮቪድ-19 እና በዓለም አቀፉ የመላላኪያ አገልግሎት መዛባት ምክንያት ‹ነጻ የታተመ መጽሐፍ አገልግሎታችንን› ለጊዜው አቋርጠናል፡፡
The New Life Mission በነጻ በሚታደሉት የክርስቲያን መጽሐፎች አማካይነት በውሃና በደም የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን መገናኘት ትችል ዘንድ ባሉት ችሎታዎች ሁሉ በተሻለው መንገድ ጌታን ለማገልገል የተሰጠ ነው፡፡ በነጻ የሚታደሉት መጽሐፎቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተመሠረቱ በመሆናቸው ሰዎች በውሃና በመንፈስ መወለድ የሚችሉበትን ተጨባጭ እውነት ቀለል ባለ ግልጥነት ያብራራሉ፡፡ በሕትመትና በኤሌክትሮኒክ ስሪቶች የቀረቡትን መጽሐፎቻችንን እንድታነብና በእነዚህ መጽሐፎች ውስጥ ተገለጠውን እውነት እንድታገኝ እናደፋፍርሃለን፡፡ በዚህ የጨለማ ዘመን ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች እውነትን እየተጠሙ ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች ወደ እግዚአብሄር ጽድቅ ለመምራት የመብራት ቤት ሆነው ማገልገል የሚችሉ የክርስቶስ ወታደሮችን እንሻለን፤ ከእነርሱም ጋር መሥራት እንፈልጋለን፡፡ የ The New Life Mission በነጻ የሚታደሉ የክርስቲያን መጽሐፎች በአጠቃላይ 65 ቅጾችን ይዘው የሰውን ዘር ደህንነት፣ የክርስቲያንን ሕይወት፣ የሺህውን ዓመትና የመንግሥተ ሰማይን ተስፋ፣ የዘላለምንም ሕይወት በሚያብራራ የእግዚአብሄር ቃል የተሞሉ ናቸው፡፡ እነዚህ መጽሐፎች የመንግሥተ ሰማይ መዝገቦች እንደተደበቁበት እርሻ ናቸው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ተብሎ የተጠራውን የከበረ መዝገብ እንድታገኝና ያለህን ሁሉ በመሸጥ ይህንን እርሻ እንድትገዛ እንፈልጋለን፡፡ በመጽሐፎቻችን አማካይነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ልንመራህ እንፈልጋለን፤ በክርስቶስም ከአንተ ጋር አብረን የጽድቅን ሥራ ልንሠራ እንፈልጋለን፡፡
The New Life Mission በ1991 በሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግ የተመሠረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ገለልተኛ የሚሽን ድርጅት ነው፡፡ ዓላማው በሥነ ጽሁፍ አገልግሎቱ አማካይነት በተለያዩ ቅርጸቶች የእግዚአብሄርን ቃል በመላው ዓለም ለእያንዳንዱ ሰው ማሰራጨት ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉምና እያንዳንዱ ሰው በውሃና በመንፈስ ዳግመኛ መወለድ እንዲችል የአገልግሎቱ ትኩረት የታተሙ መጽሐፎችን፣ ኢ-መጽሐፎችንና ኦድዮ መጽሐፎችን በማተምና በመበተን ላይ ያረፈ ነው፡፡ The New Life Mission ዋና መሥሪያ ቤቱ በሰሜን ኮርያ፤ ሴዑል ሲሆነ በዓለም ዙሪያ ከ90 በላይ በሚሆኑ አገሮች አጋር ሠራተኞች አሉት፡፡ እነዚህ አጋር ሠራተኞች ከሬቨረ. ጆንግ ጋር አብረው ግባቸውን የእግዚአብሄርን መንግሥት በመገንባት ላይ አኑረዋል፡፡
የሥነ ጽሁፍ አገልግሎት ወንጌልን በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት እጅግ ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም የሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግን ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፎች ከ90 በላይ በሆኑ ዋና ቋንቋዎች አሳትመናል፡፡ ተጨማሪ ነፍሳቶችን ወደ ጌታ ጽድቅ ለመምራትም ጠንክረን በመሥራት እንቀጥላለን፡፡ ተርጓሚና/ወይም አርታኢ በመሆን ከአገልግሎታችን ጋር እንድትቀላቀል ብታስብ እንወዳለን፡፡ ፍላጎት ካለህ እባክህ ‹‹አጋር ሠራተኛ ለመሆን ተመዝገብ›› የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግ፡፡